ለተማሪዎች በግዳጅ የሚሰጠውን ካድሬያዊ ስልጠና እና ትውልድን የማኮላሸት ሴራ አጥብቀን እናወግዛለን!

ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ
ለተማሪዎች በግዳጅ የሚሰጠውን ካድሬያዊ ስልጠና እና ትውልድን የማኮላሸት ሴራ አጥብቀን እናወግዛለን!
ላለፉት 23 ዓመታት ህወሓት/ኢህአዴግ ስራዬ ብሎ ካዳከማቸውና ጉዳዬ ከማይላቸው ዘርፎች ውስጥ የሚመደበው የትምህርት ስርዓቱ ሲሆን ይህም ከኢህአዴግ ስህተቶች ሁሉ ዋነኛው እና አሳፋሪ ተግባሩ ነው፡፡ ለሁለት አስርት አመታት ትውልዱን በማምከን በሀገሩ ተስፋ እንዲቆርጥ ከገፉት ጉዳዮችም ግንባር ቀደሙ የህወሓት/ኢህአዴግ የተምታታበት የትምህርት ፖሊሲ መሆኑም ይታወቃል፡፡ ትምህርት ለአንድ ሀገር እድገት የጀርባ አጥንት መሆኑ እየታመነ የትምህርት ስርዓቱ ሆን ተብሎ በንቀት እና በዝርክር አሰራር እንዳያድግና ጥራት እንዳይኖረው ኢህአዴግ እየተጋ አሁን ድረስ ዘልቋል፡፡ በዚህ አይነቱ አጥፊ አካሄድ ምክንያትም ሀገራችን በዓለም ደሃ ሀገራት ተርታ ቀዳሚዋ ሆናለች፡፡

የተማረ እየተገፋ በስራ አጥነት ሲንከራተት እና ለስደት ሲዳረግ በካድሬነት የስርዓቱ አገልጋይ መሆን ደግሞ በተቃራኒው...

የሰማያዊ ፓርቲ አስተባባሪዎች ፍርድ ቤት እንዳይቀርቡ ተከለከሉ

በአሸባሪነት ተከሰው የታሰሩት የሰማያዊ ፓርቲ የጋሞ ጎፋ ዞን አስተባባሪዎች ፍርድ ቤት እንዳይቀርቡ መከልከላቸውን የፓርቲው የአደረጃጀት ጉዳይ ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ተክለያሬድ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ አቶ ሉሉ መሰለ የፓርቲው የዞኑ ሰብሳቢ እንዲሁም አቶ በፍቃዱ አበበ የዞኑ ምክትል ሰብሳቢ ለዛሬ ነሃሴ 10 ፍርድ ቤት ሊቀርቡ ተቀጥረው የነበሩ ቢሆንም ፖሊስ ፍርድ ቤት እንዳይቀርቡ ተደርገዋል ሲሉ ኃላፊው ገልጸዋል፡፡

የሰማያዊ ፓርቲ የአርባ ምንጭ አስተባባሪዎች ላይ እስሩ ቀጥሏል

ከአሁን ቀደም አራት የሰማያዊ ፓርቲ የአርባ ምንጭ አስተባባሪዎች በሽብርተኝነት ስም መታሰራቸው ይታወቃል፡፡ እነዚህን እስረኞች ያሉበትን ሁኔታና የዞኑን አደረጃጀት ለመጎብኘት ከአዲስ አበባ (ከማዕከል) የድርጅት ጉዳይ ኃላፊው አቶ ብርሃኑ ተክለያሬድና የድርጅት ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ አባል የሆነው ዮናስ ከድር ለጉብኝት በሄዱበት ወቅት ሲያስተባብሩ የነበሩት አባላት ከማዕከል የሄዱት የፓርቲው አመራሮች ሲመለሱ ለእስር መዳረጋቸውን ከአካባቢው የደረሰን መረጃ ይጠቁማል፡፡ .....

እነ ወይንሸት በይግባኝ የ7 ቀን ጊዜ ቀጠሮ ተሰጠባቸው

ሐምሌ 29 ጠዋት ሜክሲኮ ልደታ ፍርድ ቤት ቀርበው በ5000 ብር ዋስ እንዲወጡ የታዘዘላቸው ወይንሸት፣ አዚዛ እና ኡስታዝ በድብቅ በተካሄደ ይግባኝ ዋሱ ተነስቶ የ7 ቀን ጊዜ ቀጠሮ ለፖሊስ ተፈቅዶለታል፡፡ በእለቱም ከሰዓት በኋላ በድብቅ ፍርድ ቤት ተወስደው የዋስ መብታቸው በይግባኝ ተገፏል፡፡ አሁን በእስር ቤት ይገኛሉ፡፡
እንዲሁም በተያያዘ ዜና ሐምሌ 30 ቀን ኢብራሂም አብዱልሰላም 5000 ብር ደመወዝተኛ ዋስ እንዲለቀቅ ተወስኖ የነበረ ቢሆንም ከ3 ሰዓታት በኋላ ፖሊስ ለይግባኝ ሰሚ ችሎት እንዲቀርብ አድርጎ ዋስትናው እንዲታገድ በማድረግ በእስር ቤት እንዲቆይ ተደርጓል፡፡

የሰማያዊ ፓርቲ የጋሞጎፋ ዞን አመራሮች ታሰሩ

አርባ ምንጭ ከተማ የሚገኙ የሰማያዊ ፓርቲ የዞኑ አስተባባሪዎች በፖሊስ ተይዘው መታሰራቸው ታወቀ፡፡ ትናንት ሐምሌ 29 ሌሊት የዞኑ ሊቀመንበር አቶ ሉሉ፣ አቶ ፈቃዱ አበበና አቶ ጌታሁን በየነ ከየ ቤታቸው በፖሊስ ተይዘው ወዳልታወቀ ቦታ የተወሰዱ ሲሆን አሁን ያሉበት ቦታ እንደማይታወቅ ከቦታው የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡

We cannot Tolerate TPLF/EPRDF’s State Terror!

Press Release by Blue Party Ethiopia / Semayawi Party- Ethiopia/

መንግስታዊ ሽብርተኝነትን የሚሸከም ትከሻ አይኖረንም!!!

ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ
ሀምሌ 3/2006ዓ/ም

ምክር ቤቱ ውሳኔዎችን አስተላለፈ

የሰማያዊ ፓርቲ ግንቦት 20/2006 ዓ.ም ባደረገው የብሄራዊ ምክር ቤት ስብሰባ የተለያዩ ውሳኔዎችን አስተላለፈ፡፡ ምክር ቤቱ በሊቀመንበሩ የቀረበውን የ6 ወር የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ያጸደቀ ሲሆን ብሄራዊ ምክር ቤቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ቀጣይ ውሳኔዎችም ተላልፈዋል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ በሊቀመንበሩ የቀረበለትን የስራ አስፈጻሚዎች የቦታ ሽግሽግም ተቀብሎ ያጸደቀ ሲሆን በሽግሽጉ መሰረትም አቶ ብርሃኑ ተክለያሬድ የአደረጃጀት ጉዳይ ኃላፊ፣ አቶ ዮናታን ተስፋዬ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ፣ አቶ ጌታነህ ባልቻ የጥናትና ስትራቴጅ ኃላፊ እንዲሁም አቶ እያስፔድ ተስፋዬ የወጣቶች ጉዳይ ኃላፊ ሆነው እንዲሰሩ አጽድቋል፡፡

ነገረ ኢትዮጵያ የግንቦት 20 ልዩ እትም ጋዜጣዋ የግንቦት 20 ‹‹ፍሬዎች›› ተዳሰውባታል፡፡

ነገረ ኢትዮጵያ የግንቦት 20 ልዩ እትም ጋዜጣዋ የግንቦት 20 ‹‹ፍሬዎች›› ተዳሰውባታል፡፡

በተለያየ ምክንያትጋዜጣዋን ኮፒ በዕለቱ ያላገኛችሁ ይኸው መረጃ ይደርሳችሁ ዘንድ በፒዲ ኤፍ ለቀናታል
PDF ያንብቧት!

ታምራት ታረቀኝ የግንቦት 20 ሰለባ የሆኑትንና ሐኪም አጥተው የሞቱትን እውቁን ሐኪም ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ያስታውሰናል፡፡
የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ስለ ግንቦት 20 ፍሬዎች የራሳቸውን እይታ ገልተውባታል፡፡
የመኢአድ ፕሬዝደንት አቶ አበባው መሃሪ፣
የሰማያዊ ፓርቲ ም/ሊቀመንበር አቶ ስለሽ ፈይሳ፣
የአረና የህዝብ ግንኙነት አቶ አብርሃ ደስታ
እንዲሁም የአንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ የፖለቲካ ጉዳይ ኃላፊ ሰሎሞን ስዩም ስለ ግንቦት 20 ይናገሩባታል፡፡
አቶ ታዴዎስ ታንቱ የግንቦት 20ን እንክርዳድ ለመመንገል ስለሚያስችለው ስልት ጽፈውባታል፡፡
ሰንደቅ አላማውና ግንቦት 20፣ ግንቦትና ግንቦታውያን፣ ግንቦት 20 የበላቸው ቀሽ ገብሩዎች፣ ግንቦት 20 እና ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ ነጻነት....እና በርካታ ጉዳዮች ተዳስሰውበታል፡፡
መልካም ንባብ!

ታላቅ የእራት ግብዣ

Pages

Subscribe to semayawiparty RSS