የሰማያዊ ፓርቲ የአርባ ምንጭ አስተባባሪዎች ላይ እስሩ ቀጥሏል

ከአሁን ቀደም አራት የሰማያዊ ፓርቲ የአርባ ምንጭ አስተባባሪዎች በሽብርተኝነት ስም መታሰራቸው ይታወቃል፡፡ እነዚህን እስረኞች ያሉበትን ሁኔታና የዞኑን አደረጃጀት ለመጎብኘት ከአዲስ አበባ (ከማዕከል) የድርጅት ጉዳይ ኃላፊው አቶ ብርሃኑ ተክለያሬድና የድርጅት ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ አባል የሆነው ዮናስ ከድር ለጉብኝት በሄዱበት ወቅት ሲያስተባብሩ የነበሩት አባላት ከማዕከል የሄዱት የፓርቲው አመራሮች ሲመለሱ ለእስር መዳረጋቸውን ከአካባቢው የደረሰን መረጃ ይጠቁማል፡፡ .....

እነ ወይንሸት በይግባኝ የ7 ቀን ጊዜ ቀጠሮ ተሰጠባቸው

ሐምሌ 29 ጠዋት ሜክሲኮ ልደታ ፍርድ ቤት ቀርበው በ5000 ብር ዋስ እንዲወጡ የታዘዘላቸው ወይንሸት፣ አዚዛ እና ኡስታዝ በድብቅ በተካሄደ ይግባኝ ዋሱ ተነስቶ የ7 ቀን ጊዜ ቀጠሮ ለፖሊስ ተፈቅዶለታል፡፡ በእለቱም ከሰዓት በኋላ በድብቅ ፍርድ ቤት ተወስደው የዋስ መብታቸው በይግባኝ ተገፏል፡፡ አሁን በእስር ቤት ይገኛሉ፡፡
እንዲሁም በተያያዘ ዜና ሐምሌ 30 ቀን ኢብራሂም አብዱልሰላም 5000 ብር ደመወዝተኛ ዋስ እንዲለቀቅ ተወስኖ የነበረ ቢሆንም ከ3 ሰዓታት በኋላ ፖሊስ ለይግባኝ ሰሚ ችሎት እንዲቀርብ አድርጎ ዋስትናው እንዲታገድ በማድረግ በእስር ቤት እንዲቆይ ተደርጓል፡፡

የሰማያዊ ፓርቲ የጋሞጎፋ ዞን አመራሮች ታሰሩ

አርባ ምንጭ ከተማ የሚገኙ የሰማያዊ ፓርቲ የዞኑ አስተባባሪዎች በፖሊስ ተይዘው መታሰራቸው ታወቀ፡፡ ትናንት ሐምሌ 29 ሌሊት የዞኑ ሊቀመንበር አቶ ሉሉ፣ አቶ ፈቃዱ አበበና አቶ ጌታሁን በየነ ከየ ቤታቸው በፖሊስ ተይዘው ወዳልታወቀ ቦታ የተወሰዱ ሲሆን አሁን ያሉበት ቦታ እንደማይታወቅ ከቦታው የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡

We cannot Tolerate TPLF/EPRDF’s State Terror!

Press Release by Blue Party Ethiopia / Semayawi Party- Ethiopia/

መንግስታዊ ሽብርተኝነትን የሚሸከም ትከሻ አይኖረንም!!!

ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ
ሀምሌ 3/2006ዓ/ም

ምክር ቤቱ ውሳኔዎችን አስተላለፈ

የሰማያዊ ፓርቲ ግንቦት 20/2006 ዓ.ም ባደረገው የብሄራዊ ምክር ቤት ስብሰባ የተለያዩ ውሳኔዎችን አስተላለፈ፡፡ ምክር ቤቱ በሊቀመንበሩ የቀረበውን የ6 ወር የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ያጸደቀ ሲሆን ብሄራዊ ምክር ቤቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ቀጣይ ውሳኔዎችም ተላልፈዋል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ በሊቀመንበሩ የቀረበለትን የስራ አስፈጻሚዎች የቦታ ሽግሽግም ተቀብሎ ያጸደቀ ሲሆን በሽግሽጉ መሰረትም አቶ ብርሃኑ ተክለያሬድ የአደረጃጀት ጉዳይ ኃላፊ፣ አቶ ዮናታን ተስፋዬ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ፣ አቶ ጌታነህ ባልቻ የጥናትና ስትራቴጅ ኃላፊ እንዲሁም አቶ እያስፔድ ተስፋዬ የወጣቶች ጉዳይ ኃላፊ ሆነው እንዲሰሩ አጽድቋል፡፡

ነገረ ኢትዮጵያ የግንቦት 20 ልዩ እትም ጋዜጣዋ የግንቦት 20 ‹‹ፍሬዎች›› ተዳሰውባታል፡፡

ነገረ ኢትዮጵያ የግንቦት 20 ልዩ እትም ጋዜጣዋ የግንቦት 20 ‹‹ፍሬዎች›› ተዳሰውባታል፡፡

በተለያየ ምክንያትጋዜጣዋን ኮፒ በዕለቱ ያላገኛችሁ ይኸው መረጃ ይደርሳችሁ ዘንድ በፒዲ ኤፍ ለቀናታል
PDF ያንብቧት!

ታምራት ታረቀኝ የግንቦት 20 ሰለባ የሆኑትንና ሐኪም አጥተው የሞቱትን እውቁን ሐኪም ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ያስታውሰናል፡፡
የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ስለ ግንቦት 20 ፍሬዎች የራሳቸውን እይታ ገልተውባታል፡፡
የመኢአድ ፕሬዝደንት አቶ አበባው መሃሪ፣
የሰማያዊ ፓርቲ ም/ሊቀመንበር አቶ ስለሽ ፈይሳ፣
የአረና የህዝብ ግንኙነት አቶ አብርሃ ደስታ
እንዲሁም የአንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ የፖለቲካ ጉዳይ ኃላፊ ሰሎሞን ስዩም ስለ ግንቦት 20 ይናገሩባታል፡፡
አቶ ታዴዎስ ታንቱ የግንቦት 20ን እንክርዳድ ለመመንገል ስለሚያስችለው ስልት ጽፈውባታል፡፡
ሰንደቅ አላማውና ግንቦት 20፣ ግንቦትና ግንቦታውያን፣ ግንቦት 20 የበላቸው ቀሽ ገብሩዎች፣ ግንቦት 20 እና ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ ነጻነት....እና በርካታ ጉዳዮች ተዳስሰውበታል፡፡
መልካም ንባብ!

ታላቅ የእራት ግብዣ

‘መድረክ’ እናመሰግናለን

‘መድረክ’ እናመሰግናለን

ሰማያዊ ፓርቲ ዛሬ በመድረክ ሰልፍ ላይ የመድረክን ጥሪ አክብሮ የተገኘ ሲሆን በሰልፉም ላይ የህዝብን ጥያቄ በማስተጋባት አጋርነቱን አሳይቷል፡፡ ይህን ሰልፍ ላዘጋጀው እና የተቃውሞ ድምፃችንን እንድናሰማ ሁኔታዎችን ላመቻቸው የፓርቲዎች ስብስብ 'መድረክ' ምስጋና ልናቀርብ እንወዳለን፡፡

የዜጎችን ጥያቄ በጥይት ማስቆም አይቻልም

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!

ሰማያዊ ፓርቲ!

May 24, 2014 MEDREK's demonstration; Blue Party(semayawi) taking part!
Killing citizens in anyway can never be justifiable!

ታላቅ የእራት ግብዣ ከሰማያዊ

ሰማያዊ ፓርቲ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያደረገ ባለው ፖለቲካዊ ትግል በፍርሀት ድባብ ውስጥ ተውጦ የነበረውን ህዝብ የጨለማ ድባብ እየገፈፈው ይገኛል፡፡ በዚህ ስራውም የብዙ ታላላቅ ምሁራንን እና ወጣቶችን ቀልብ መሳብ ችሏል፡፡ በመሆኑም ፓርቲው ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎችን ያሳካ ዘንድ ብሎም አሁን ካለበት የተሻለ ተንቀሳቅሶ ተፎካካሪና ተወዳዳሪ ፓርቲ ይሆን ዘንድ ገንዘብ ያስፈልገዋል፡፡ ገንዘቡን ሊያገኝ የሚችለው ደግሞ ከአበላትና ደጋፊዎች መሆኑ ሀቅ ነው፡፡ በመሆኑም ግንቦት 23 ቀን 2006 ዓ.ም በአዲስ ቪው ሆቴል ታላቅ የእራት ግብዣ ፕሮግራም ደግሶ ይጠብቅዎታል፡፡የእራት ግብዣው መግቢያ ካርዶችም የተዘጋጁ ሲሆን እነዚህም ባለ አምስት መቶ ባለ አንድ ሺህ፤ባለ ሶስት ሺህ፤ባለ አምስት ሺኅ እና ባለ አስር ሺህ ብር ናቸው፡፡እርስዎም የእራት ግብዣውን ካርድ በመግዛት ሰማያዊ ፓርቲን እያገዙ ወደ ነጻነት ይጓዙ፡፡ ባለ አስር ሺህ ብር ካርድ በቁጥር ጥቂት ስለሆነ ባለ አምስት ሺህና ሶስት ሺህ አማራጭ መኖሩን እንዳይዘነጉ፡፡ በእራት ግብዣው ላይ የተከበሩና ታላላቅ ሰዎች፤ተጋባዥ እንግዶች፤ታላላቅ ፖለቲከኞች፤ገጣሚያንና ጋዜጠኞች ይገኛሉ፡፡እንዲሁም የተለያዩ አዝናኝ ፕሮግራሞች፤ጨረታዎችና ታዳሚን ሊያዝናኑ የሚችሉ ለየት ያሉ ጨዎታዎች ይቀርቡበታል፡፡ በዚህ የእራት ግብዣ ላይ በመገኘት እየተዝናኑ፤በኢትዮጵያዊ ጨዋነት እየተጎራረሱ ስለ ሀገርዎ እጣ ፈንታ በመሶብ ዙሪያ ይነጋገሩ፡፡ የመግቢያ ካርዶችን ከአስተባባሪዎች፤ከአባላትና ከአመራሮች ማግኘት የሚችሉ ሲሆን ከሀገር ውጭ የምትኖሩ ወገኖቻችን የመግቢያ ካርዱን ለወዳጅ ዘመድ መግዛት የሚቻል በመሆኑ ይህን በአይነቱ ለየት ያለና ለነጻነት የሚከፈል ውድ ስጦታ ወዳጅ ዘመድዎን እንዲጋብዙ ስንል ጥሪ እናቀርባለን፡፡ አያይዘንም የእራት ግብዣው ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ክፍት መሆኑን እንገልጻለን፡፡
ለበለጠ መረጃ፡-ሰማያዊ ፓርቲ
ስልክ ቁጥር-+251 911 679223
+251 931 153809
+251 11 8 592950
አቢሲኒያ ባንክ አራዳ ቅርንጫፍ የባንክ ሂሳብ ቁጥርC/619
E-mail info@semayawiparty.org
www.semayawiparty.org

Pages

Subscribe to semayawiparty RSS